አንተ ብቻ ና || ዘማሪት ህሊና ዳዊት || Gospel Singer Helina Dawit @ARC
Published 2024-05-04
This is an official YouTube channel of Pastor Henok Mengistu (Singele). You can subscribe and reach out to the teachings, preachings and life changing services of his ministry.
#pastor_HenokMengistu #መጋቢ_ሄኖክ_መንግስቱ
All Comments (21)
-
ይህች ልጅት በዘመኑ ከበዛው ከግርግሩ መሀል አንዴት አምልጣ ይህንን ድንቅ መልአክት አንደተቀበለች ይገርመኛል። Let God multiply this amazing blessing! Amen!!!!
-
ብትሰጠኝ ምንም ነገር ሀገር ምድሩ ቢነጋገር በዚያ ብዙ አልገኝም ከአንተ በልጦ አይሞቀኝም በዘመኔ ላትሆን ተራ መሀላ አለኝ ከነፍሴ ጋራ እኔ አንተኑ ተርቤያለው አንተን ደግሞ ጠግቤያለው አብርሀም ቤት ይሳቅ ሲመጣ መቼ ተተካ ያንተ ቦታ እጅ አይበልጥም ከፊት ፈገግታ አይቀልም ሰጪ ከስጦታ ሙሴ ከነዓንን ባይወርስም አለ እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም ማጉረምረም ማዘን መች ቻለበት ማር እና ወተት ሆነህለት ❤❤❤❤
-
ምን አይነት መረዳት ነው ። ዝማሬዎች ሀሉ ሰው ፣ቁስ፣ ምድር ተኮር በሆኑበት በዚህ ዘመን ፤ ሰማያዊ ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚታይበት ፣ ክርስቶስ ተኮር ሲሆን ከዚህ በላይ ምን ደስታ አለ? ክብሩን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወሰድ። አሜን።
-
በየደቂቃው እየመጣው የምሰማው እኔ ብቻ ነኝ
-
ጌታ ሆይ ለኔ ይሄ መንፈስ ያስፈልገኛል 😭😭😭😭😭
-
ይህን የአምልኮ ዘይቤ እንደ እኔ ነፍቆት የነበረ ማነው? ጉባኤው ዝግ ብሎ በፀሎት መንፈስ መልእክት መስማት የጥንቱ የቤተክርስትያን ምርኮ እየተመለሰ ይመስለኛል፡፡ ጊዜው ይጠብቅ እንጂ ለካ እግዚአብሔር ትውልድ አለው ፡፡
-
ብዙ ግዜ ኮሜንት ለመፃፍ ጎበዝ አይደለሁም ለዚኛው መዝሙር ግን ዝም ማለት አልቻልኩም መንፈሳዊ ነገር ሁሉ በእግዝያብሄር ቃል መሰረቱን ሲያረግ ስጋን አልፎ ልብን ይነካል ከሰማሁ ሰዓት ጀምሮ እንባዬ እንደመጣ ነው😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭 እህቴ እግዚያብር ይባርክሽ ፀጋውን ያብዛልሽ !!
-
ብትወድ በሀይለኛው ንፋስህ ብትወድ በነበልባል እሳትህ ብትወድ ዝም ባለው ፀጥታህ ብተወድ በትንሿ ኮሽታህ ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና
-
ልሳንሽን ካጣፈጠው ጌታሽ ጋር ይለቅ ዘመንሽ!!
-
አሁን ጊዜው ነው እሱ ብቻ ሊዘመር ሊወራ ሊተረክ !!! ኢየሱስ ጌታ ነው!!!
-
😭😭😭 የሚያሳስበኝ ይህ መዝሙር ስንቶቻችን ይገባን ይሆን የሚለው ነው!!!
-
ምን አይነት መረዳት ነው ጌታ ለዘላለም ይባርክሽ እልፍ ሁኝ እንዳንቺ ያሉ ይብዙልን
-
ሰማዩ ሚናፍቀኝ አንተ እዚያ ስላለህ ነው
-
እንደ ዳንኪራ ቤት ከዝላይ ከጭፈራ ከዳንስ ከወላይትኛ ጭፈራ በአምልኮ ስም ተዋርደን አፍረንነበር !!! ጌታ ይባርክሽ !! ድሮ እኮ ጴንጤ ይከበር ይታመን ነበር ዘንድሮ አንገት ደፋን
-
ልቤ ወደ ጌታዬ ፈሰሰ ፣፣፣ ተባረኪ የኔ ውድ እህት በሰማሁት ሁሉ ቁጥር ፀልይ ፀልይ ይለኛል እናም እንበረከክና አለቅሳለሁ ፨ብትወድ በሀይለኛዉ ንፈስ ፨ ብትወድ በነጎድጎድ እሳት፨ ብትወድ ፦፦፦፦፦፦ ብቻ አንተ ና ብቻ አንተ ና ፣አንተ ብቻ ና ብቻ ፣ አንተ ብቻ ና ።......።።።በቃ ተባረኪ ምን ልበል
-
ጌታኮ በየዘመናቱ ሰው አለው እልፍ ሁኝልን ተባረኪ❤❤❤
-
እሄን መዝሙር ሰሰማው airport ውስጥ transit አርጌ ሌላኛዉን plane እየጠበኩ ባለሁበት ሰዓት ነዉ የሰማሁት ለፅፈው ባልችልም አሁን ለይ የመጣሁበት አና በዚች ሰዓት ያለሁበት አና ደሞ እየህድኩበት yalewun ሁኔታ የዘምረቺው ነው የመስለኝ እንደዚ ጉልበት ሰቶኝ አቅም ሆኖኝ asinantogn ሚያቅ መዝሙር ያለ Aymeslgnim, መላኮች በሰው መልክ አብርሃም ቤት እንደገቡት እኔ ልብ ወስጥ በመዝምር መልክ የገባ ነዉ የመሰለኝ
-
ህሉዬ ይህ መንፈስ፣ ይህ መረዳት፣ይህ ፍለጋ አይወሰድብሽ ! አንቺ እንደ ቃሉ አሁን ላለችው የምድሬ ቤተክርስቲያን የተሰጠሽ ስጦታ ነሽ ፣ በምሳሌነትሽ ቀጥይ፣ ፀጋው ይብዛልሽ!
-
ስጠኝ ምንም ነገር ግን አንተን የሚከተል ሀሌሉያ🥰🥰🥰
-
ለካስ ብዙ ተርበንና ተጠምተን ነበር ጌታ ኢየሱስ ሆይ ያማረውን ዜማ እና ቅኔ ይፍሰስልህ እህቴ ህሊና በብዙ ተባረኪ የፀጋው ባለቤት የተመሰገነ ይሁን አሜን ።